Tender Detail

Tender Details

  • Company Waliya Capital Goods Finance Business S.C (ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ቀበሌ 10 ከአጅፕ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ፀደይ ባንከ የሥልጠና፣ የጥናትና የምርምር ማዕከል ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 እና አዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ፒያሳ አትክልት ተራ ሴካ የንግድ ማዕከል ህንፃ ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 001 ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0920493114
  • Websitehttps://waliyacapital.com/
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየአጠቃላይ ዋጋውን 2%
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ/ማ ዋናው መ/ቤት ለአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎት የሚውሉ 09 (ዘጠኝ) ላፐቶፕ ኮምፒዩተር /LAPTOP COMPUTER/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Waliya Capital Goods Finance Business S.C (ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር)


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ/ማ ዋናው መ/ቤት ለአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎት የሚውሉ 09 (ዘጠኝ) ላፐቶፕ ኮምፒዩተር /LAPTOP COMPUTER/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉና ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች በመሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጨረታው መመሪያ፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የሥራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ወይም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የአጠቃላይ ዋጋውን 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ በዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ትክክለኛ ስም በማሰራት ተወዳዳሪዎች ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. አሸናፊው ማሸነፉ በተገለፀበት ጊዜ ውል ከያዘ በ30 (ሰላሳ) ቀናት ወስጥ ዕቃውን ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  4. ጨረታውን በወትቱ ዋጋ ሞልቶና አጠናቆ ያላቀረበ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  5. የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ኮርፖሬት ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 306 በመትረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛ ቀን በዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ/ማ ዋና መ/ቤት ባህር ዳር እስከ ቀኑ በ6፡00 ሠዓት ድረስ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሣቸው ፈቃድ ካልተገኘ አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን ከመክፈት አይታግድም፡፡
  8. የማስረከቢያ ቦታው ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው የዋልያ የካፒ/ዕ) ፋይ ንግድ ሥራ አ/ማ ዋና መ/ቤት ነው።
  9. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582206728/ 0582205359 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  11. አድራሻው በአብክመ ዋልያ የካፒ/ዕቃ ፋይ/ንግድ ሥራ አ/ማ ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 10 ከአጅፕ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት የፀደይ ባንክ የሥልጠና የጥ/የምር ማዕከል ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ነው።

 

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ/ማ

 

Save Tender