እልልታ ውመን እት ሪስክ ድርጅት በአጠቃላይ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራር መርሆች (GAAP) መሰረት የተከናወኑ የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ህጋዊ እውቅና ባላቸው የአዲት ድርጅቶች ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
እልልታ ውመን አት ሪስከ
ምርመራ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅት: እልልታ ውመን አት ሪስከ (EWAR)፣ ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው::
የአገልግሎቱ ዝርዝር: እልልታ ውመን እት ሪስክ ድርጅት በአጠቃላይ ተቀባይነት ባለው የሂሳብ አሰራር መርሆች (GAAP) መሰረት የተከናወኑ የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ህጋዊ እውቅና ባላቸው የአዲት ድርጅቶች ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
የሚመረመረው የጊዜ ገደብ: እንደ ኢ.አ ከጃንዋሪ 01 ቀን 2025 ዓ.ም. እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2025 ዓ.ም ያለውን የአንድ ዓመት የድርጅቱን የሂሳብ እንቅስቃሴ ያጠቃልላል፡፡
ተፈላጊ የኦዲተር መስፈርቶች: በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመወዳደር የምትፈልጉ አዲተሮች/የአዲት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት እና ህጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
ተጫራቾት-
ህጋዊ ፈቃድ: ለኦዲት ስራ የሚውል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ሀጋዊና የታደሰ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ።
የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ: የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን እና ተገቢውን ማረጋገጫ ማቅረብ፡፡
ሙያዊ እውቅና: የፋይናንስ እና የኦዲት ሥራ እውቅና/ምስከር ወረቀት ያለው ያላት መሆን፡፡
ተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ምዝገባ: ለተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) የተመዘገቡ መሆን እና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ፡፡
የጨረታ አቀራረብ እና ቀነ-ገደብ፡-
ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ: ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
የማመልከቻ ቦታ: ድርጅቱ ዋና ቢሮ፣ አዲስ አበባ ልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጥቁር አንበሳ የኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ፊት ለፊት ኤስ አይ ኤም (SIM) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ።
አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች፡-
የጨረታ ሰነድ ይዘት እና አቀራረብ: ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋቸውን ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ጨምሮ እና የሂሳብ ምርመራውን የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ በግልጽ በመግለጽ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የዋጋ ስቀራረብ ገደብ: ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
ለተጨማሪ መረጃ:-
ለተጨማሪ ማብራሪያዎች በሚከተሱት ስልክ ቁጥሮች መደወል ይቻላሱ፡- 0960277153/0911310954 0911312916
የእልልታ ውመን አት ሪስክ (EWAR)
