በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ
የግንባታ ጨረታ ማስተወቂያ
የጨታ ቁጥር 002/2018
በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን በአካል በመምጣት ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ሎት |
የስራው ዓይነት |
የግንባታ ጊዜ (በቀን) |
የጨረታ አየር ላይየሚቆይበት ቀን |
ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን |
የጨረታ ሰነድ የሚገባበት ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
የሻይ ቤት እድሳት፤ የካርድ ከፍል እድሳት! የነባሩ ህንጻ የውጭ ግድግዳ የቀለም ቅብ እድሳት |
45 ቀን |
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት |
BC7 እና ከዚያ በላይ |
50,000 ብር በባን (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና |
ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16 ኛው ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስክ 4፡00 ሰዓት |
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት ከ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 በወ/ሮ በለጥሻቸው የሕህዝብ ጤና ጣቢያ አዲስ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል፡፡ |
1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ወይም የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው ግዴታችን እየተወጡ መሆናቸውን የሚገልጽ እና በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል የሚያቀርቡ ሆነው ጨረታውን አሸናፊ ከሆኑ ግን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ውል ከማሰራቸው በፊት ማቅረብ የሚችሉ ፤ የ2018 ፈቃድ ያደሱም ቢሆኑም ሁሉም ተጫራቶች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው/ ከሁለቱም ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፤ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡ በልደታ ከፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አፈፃፀም ከ 75% በላይ መሆኑን የሚገልፅና መልካም አፈፃፀም (Good Performance) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ሁሉም ተወዳዳሪ ተቋራጮች ቀድሞ ለሰሩት ፕሮጀከት ከሰሩበት ተቋም የቅርብ ጊዜ የመልካም የስራ አፈፃፀም ማቅርብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በልደታ ከፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original)፤ የማይመለስ ቅጂ (copy) የማይመለስ ብር 200 ብቻ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ባለው መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በልደታ ከፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDTIONAL BANK GUARANTEE ከላይ በተጠቀሰው የብር መጠን በልደታ ከፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድን በጨረታው ሰነድ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት የመጫረቻ ሰነድ በማዘጋጀት፡-
6. ውድድሩ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴከኒካል አንድ ኦርጂናል እና ቴከንካል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና ፋይናንሽያል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BIDSECURITY) ለብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባ ችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት በልደታ ክፍለ ከተማ በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከላይበተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት (ሙሉ በሙሉ ባይገኙ የሚከፈት ይሆናል)፡፡
7. አሰሪው መ/ቤት አሸናፈው ካሸነፈበት አጠቃላይ ስራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡ እና የግንባታ
ላይቱን ማየት ይመከራል፡፡
9. የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማክበር፣ በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶች በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፤በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Bate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡ በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የድርጅቱ የስራ ልምድ እና ማንኛውም በቴከኒካል የተጠየቁ ዶከመንቶችን አሰሪ መስሪያ ቤት ኦሪጅናል ዶከመንት የመጠየቅ እና ዶክመንቶቹን ከሰጠው አካል የማጣራት መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ግዥ ከፍል በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
12. አድራሻ:- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ አብነት የሚወስደው መንገድ ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ፊት ለፊት ዋናውን አስፓልት ተሻግሮ 100 ሜትር ገባ ብሎ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በልደታ ክፍስ ከተማ ጤና ጣቢያ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የመ/ቤቱ ስልክ 011-8-54-92-37
በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ
