Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2018

 

በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የእቃው አይነት /ስም/

ብዛት

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

1

ላተራል

7

 

 

 

 

የቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ከህንፃው በስተጀርባ

2

ተሽከርካሪ ወንበር

103

3

ፋይል ካቤኔት

9

4

ጠረጴዛ

2

5

የእንግዳ ወንበር

6

6

የፐላስቲክ ወንበር

30

7

የተለያየ ጣውላ

43

8

ኮመኪኖ/ድሮር

7

9

የላተራል በር

53

10

የላተራል መደርደሪያ

30

11

የተገነጣጠለ የላተራል መደርደሪያ

40

12

ራክ

6

13

የነዳጅ በርሜል

4

15

በድምር

340

 

 

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 506 የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ሞልተው በታሸሃ ኤንቨሎፕ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ ቢያስቀምጥሙ ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ዋጋ መሆኑን ተገንዝበው የማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በስተጀርባ ንብረቱን በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
  6. የጨረታው አሸናፊዎች ውል ከፈፀሙበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ፈፅመው ሙሉ እቃውን ማንሳት አለባቸው።

 

አድራሻ ፡- ገርጂ እንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ከአስፓልቱ 500 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ከ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506

ስልክ ቁጥር፡- 0116394235/0116394207

 

የቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender