ሄልፕ ፎር ፐርሰንስ ዊዝ ዲሴቢሊቲስ ኦርጋናይዜሽን (ኤች.ፒ.ዲ.ኦ) ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን እ.ኤ.አ. የ2025 በጀት ዓመት በታወቀ የውጪ ኦዲተር ሂሳቡን ለማስመርመር ይፈልጋል።
Help for persons with Disabilities Organization (HPDO) (ሄልፕ ፎር ፐርሰንስ ዊዝ ዲሴቢሊቲስ ኦርጋናይዜሽን) (ኤች.ፒ.ዲ.ኦ)
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ሄልፕ ፎር ፐርሰንስ ዊዝ ዲሴቢሊቲስ ኦርጋናይዜሽን (ኤች.ፒ.ዲ.ኦ) ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን እ.ኤ.አ. የ2025 በጀት ዓመት በታወቀ የውጪ ኦዲተር ሂሳቡን ለማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- የ2018 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
- በሂሳብ ምርመራ በቂ ባለሙያና የሥራ ልምድ፣
- የታክስ መለያ ቁጥር/ቲን
- ለአገልግሎት የሚጠየቅ የገንዘብ መጠን፣ የሚከናወን የኦዲት ሥራ ዝርዝር እና ሥራውን ሠርቶ ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የሚፈጀውን ጊዜ።
ከላይ የተመለከተውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተመለከተው አድራሻ የተጠየቁትን መስፈርቶች በግልጽ የሚያሳዩ መረጃዎችን በሰነድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በሥራ ሰዓት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታውም በስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 9፣ አራት ኪሎ ቅዱስ ፕላዛ ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ
ሞባይል: 0911-24-18-03
ሄልፕ ፎር ፐርሰንስ ዊዝ ዲሴቢሊቲስ ኦርጋናይዜሽን
(ኤች.ፒ.ዲ.ኦ)
