Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር ARHC 003/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1- መድኃኒት እና የህክምና እቃዎች
  • ሎት 2- የቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመወዳደር የምትፈልጉ ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች፡-

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የሚቀርብ ማስረጃ።
  2. የመንግስት የግዢ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 መግዛት ይችላሉ።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውላል።
  7. ተጫራቾች የዶክመንታቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ውል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ እንደተነገራቸው ቀርበው ውላቸውን ለመፈጸም 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. የጨረታ ሳጥን የሚዘጋው ጨረታው በወጣ 11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  13. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መመለስ ይኖርባቸዋል።
  14. ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ማህበራት በመመሪያው መሰረት በሚሰሩት ምርት ወይም ግብአት ላይ ብቻ ሰነድ ያለክፍያ መውሰድ ወይም መጫረት ይችላሉ።
  15. ጤና ጣቢያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ በተለምዶ ጫካ ሜዳ በሚባለው ሜይዴይ ትምህርት ቤት ገባ ብሎ ነባር ቀበሌ 32።

ስልክ ቁጥር 011 278 6801/ 011 275 8961

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 06 አዲስ ራዕይ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender