Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2018

 

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና
  • የኮብራ መኪና መለዋወጫ ሞዴል HZJ 80 0032519

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና TIN ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሁለት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን ከ ቀነ 6፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተብሎ ተለይቶ ኦሪጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ለ30 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ከላይ የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 11ኛው ቀን በ6:00 ይታሸግና በ6፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የኤሌክትሮኒክስ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ በዕለቱ የሚከፈት ይሆናል።
  8. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀን ቅዳሜና ዕሁድን ጨምሮ ነው።
  9. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሣብ መቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በሚለው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በሲ/ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማትኤጄንሲ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር1000351753707 ገቢ በማድረግ በኤጀንሲው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል።
  11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሣሰቢያ፡- ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሀሣብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ /የቀረበ/ ተጨማሪ ሰነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል።

በመወዳደሪያ ሠነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሀሣብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የማወዳደሪያ ሃሣብ ይሰረዛል፡፡አጠቃላይ የዕቃው ዝርዝርና ሲፒኦ ማስያዥያና ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡በጨረታው ሰነድ ላይ ከጠቀመጠው እሰፔክ ውጪ ተጨማሪ አስፔክ በእስክሪፕቶ መጻፍ አይፈቀድም ይህ ሆኖ ቢገኝ ግን ከውድድሩ ውጪ የምናደረግ መሆኑን እንገልጻለን።

አድራሻ፡ ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 221 7860 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ

Save Tender