Tender Detail

Tender Details

  • Company የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-35-88-67-18
  • Website
  • Deadline18 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2025-12-18 00:00:00
  • Categories Construction Machinery

የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው መንገድና ሎጂስቲከስ ጽ/ቤት በወረዳው ካፒታል በጀት መንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት የሚውሉ የግሬደር፣ የኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሲኖ ትራክ እና ሻወር ትራክ ማሽኖችን በኪራይ ለመቅጠርይፈልጋል፡፡

የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሌቃ ዱላቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው መንገድና ሎጂስቲከስ ጽ/ቤት በወረዳው ካፒታል በጀት መንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት የሚውሉ የግሬደር፣ የኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሲኖ ትራክ እና ሻወር ትራክ ማሽኖችን በኪራይ ለመቅጠርይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ ያላችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ እናስታውቃለን፡፡

አስፈላጊ መስፈርቶች:

1. የማሽነሪ ኪራይ ንግድ ፈቃድ የ2018 ዓ.ም የታደሰ

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆናችሁ

3. የ2017/18 ዓ.ም ግብር መከፈላችሁን የሚገልጽ ከገቢዎች ባለስልጣን የሚቀርብ ደብዳቤ

4. ተጫራቾች የማሽኖቹን የምርት ስም፤ የተመረተበትን ሀገር፣ የሞዴል ቁጥር እና የተመረተበትን ዓመት በግልጽ በመጻፍ ማቅረብ አለባቸው።

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆን

6. ለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽኖች ዝርዝር፡-

1. ግሬደር ሞዴሉ 140H/K/G እና የፈረስ ጉልበቱ 185 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ ከ2017 ዓ.ም በፊት ያልሆነ፡፡

11. ኤከስካቫተር ሞዴሉ CL/DL 325 እና በላይ የሆነ እና የፈረስ ጉልበቱ 318 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ ከ2017 ዓ.ም በፊት ያልሆነ።

III. ሲኖ ትራክ ሞዴሉ 325 እና በላይ የሆነ፣ የፈረስ ጉልበቱ 336 እና በላይ የሆነ፣ የምርት ዓመቱ ከ2020 ዓ.ም በፊት ያልሆነ፣ ከፍያው እንደ ርቀቱ (0-5 ኪ.ሜ, 5-10 ኪ.ሜ, 10-15 ኪ.ሜ እና 15-20 ኪ.ሜ) የሚከፈል ሲሆን ተጫራቾች ዋጋውን በዝርዝር መግለጽ አለባቸው፡፡

IV. ሮለር ሞዴሉ BW 14 AD እና ከዚህ በታች ያልሆነ የፈረስ ጉልበቱ 160 እና በላይ የሆነ

V. ሻወር ትራክ ሞዴሉ 325 እና በላይ የሆነ የፈረስ ጉልበቱ 336 እና በላይ የሆነ የምርት አመቱ 2017 G.C እና ከዚህ በፊት ያልሆነ።

7. የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ማቅረብ የሚችል እና ማሽኑ ጕዳት ከደረሰበት በራሱ ወጪ በአስር (10) ቀናት ውስጥ መጠገን ወይም ተመሳሳይ ማሽን መተካት የሚችል፡፡

8. የኪራይ ቦታ አድራሻ በአግባቡ የተረጋገጠ የወረዳ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር እና ስልክ ቁጥር ማቅረብ አለበት፡፡

9. ተጫራቾች የዚህን ስራ ልምድ የሚያሳይ ማስረጃ ከ2015 ዓ.ም በፊት ማቅረብ አለባቸው (አዲስ ፈቃድ አይታሰብም)።

10. ተጫራቾች እንደ ምግብና መጠጥ፣ ማረፊያ ቦታ፣ ማሽኑን በስራ ቦታ መጠበቅ፣ ነዳጅ እና ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ።

11. የማሽኖቹን የትራንስፖርት ወጪ (መጫንና ማውረድ) ተጫራቾች በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡

12. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ተጫራቹ የድርጅቱን ስነ-ምግባር ካላከበረ የጨረታ ማስከበሪያው ያለ ምንም ጥያቄ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ማሸነፉን ካወቀ በኋላ ማሽኑን በተስማማበት ጊዜ ካላቀረበ የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያወ-ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡

13. የውል ማስከበሪያው ከጠቅላላው ዋጋ 10% የሚያስይዝ ሲሆን የውል ማስከበሪያው ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ተረጋግጦ ርክከቡ ከተፈጸመ በኋላ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን የሌቃ ዱለቻ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender