Tender Detail

Tender Details


የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት፣ በውስጥ ገቢ በጀት እንዲሁም በልዩ ልዩ የበጀት ምንጮች የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ የጽዳት ዕቃዎች የስፖርት ማቴሪያሎች፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የመኪና ጎማ እና መለዋወጫዎች እንዲሁም የሰራተኞችን የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግባት ይፈልጋል፡፡

የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት፣ በውስጥ ገቢ በጀት እንዲሁም በልዩ ልዩ የበጀት ምንጮች የጽህፈት መሳሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ የጽዳት ዕቃዎች የስፖርት ማቴሪያሎች፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የመኪና ጎማ እና መለዋወጫዎች እንዲሁም የሰራተኞችን የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግባት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት -

1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና የሚያቀርበው ዋጋ ከ200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ሰርተፊኬት እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሒሳብ ቁጥር 1000053977425 በመከፈል የባንከ ደረሰኝ ይዞ በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 ተከታታይ ቀናቶች መግዛት ይችላሉ፤

3. የጨረታ ማስከበሪያ 2% ከባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችል፣ ካሽነፈ በኋላ ያሸነፈበትን 10% የውል ማስከበሪያ ከባንክ በተመሰከረለት (CPO) የጨረታው አሸናፊነት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም አድራሻ፣ የሚመለከተው አካል ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ እና የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ፣ የስሌት ስህተት ሳይኖርበት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ ዋና እና ኮፒ በመለየት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ በሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግፋ/ን/አስ/ር በመሪ ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር5 ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡

5. ጨረታው የሚጸናበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ተከታታይ ቀናቶች ይሆናል፡፡

6. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣበት በ15ኛው ቀን 4፡00 ይታሸጋል፡፡

7. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣበት በ15ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

9. ኮሌጁ ሳምፕል የሚያቀርብባቸውን ዕቃዎች የመጫረቻ ዋጋ ከመሞላቱ በፊት የቀረበውን ሳምፕል ማየት ያስፈልጋል

10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 0921264905/ 0920199394/0912424640/

የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

Save Tender