በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽግቤት በስሩ ከሚገኙ የወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በማሰባሰብ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድብ በመከፈል ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/03/2018
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽግቤት በስሩ ከሚገኙ የወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በማሰባሰብ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድብ በመከፈል ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 ቁርጥራጭ ብረታብረቶችና የተሽከርካሪ ማሽነሪ አካላት፣
ሎት 2 የተሽከርካሪ ጎማዎች፣
ሎት 3 የትምህርት ስርዓታቸው የተቀየረ የመማሪያ መጽሃፎችና ወረቀቶች እና
ሎት 4 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች
1. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
3. ተጫራቾች በሎት የተመደቡትን የንብረቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል ከገንዘብ ጽ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት የሎት ምድብ አይነት ጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመቀበያ ደረሰኝ በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /original/ የመወዳደርያ ሰነዳቸው ጋር በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የሞሉትን ኦርጂናል የመወዳደሪያ የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ22 | 03 /2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 07/04/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ማስገቢያው ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ07/04/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በጨፋ ሮቢት ከተማ የሚገኙ የእ/ፉ ወረዳ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ባሉበት ቦታ በመሄድ በአካል ማየት ይችላሉ፡፡ ለአሸናፊ ተጫራቾች ርክክብ የሚፈፀመውም ንብረቶቹ ባሉበት ቦታ ነው፡፡
9. ተጫራቶች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ውጭ የመሆን ጥያቄ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረቶች ሙሉ ከፍያ የጨረታ አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ከፍያ በመከፈል ንብረቶችን ማንሳት አለባቸው፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ከፍያውን ፈፅመው ካላነሱ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
11. ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ ስም ከነአያት፣ ፊርማና ስልከ ቁጥር መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
12. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0334490061 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብ/ዞን
የአርጡማ ፉርሲ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
