የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ፤ ህንፃ ሥራ እንዲሁም መንገድ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC/RC -4) የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በሃዋሳ ኤርፖርት ለበረራ ትምህርት ከፍል መምህራንና ተማሪዎች የስፖርት ሜዳ እና የፍተሻ ክፍል ግንባታ ስራ (Construction of Sport Field and Security Screening Room project for PTS Instructors and students at Hawassa Airport) ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቶች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT -T590
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ፤ ህንፃ ሥራ እንዲሁም መንገድ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC/RC -4) የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በሃዋሳ ኤርፖርት ለበረራ ትምህርት ከፍል መምህራንና ተማሪዎች የስፖርት ሜዳ እና የፍተሻ ክፍል ግንባታ ስራ (Construction of Sport Field and Security Screening Room project for PTS Instructors and students at Hawassa Airport) ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቶች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT T590 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር (250,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው። የፕሮጀከቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 180 ተከታታይ ቀናት ይሆናል::
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፐ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታኅሣሥ 16 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ-ሜይል: WoldeM@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
