Tender Detail

Tender Details

  • Company አማኑኤል ፀጋ የከተማ ንግድ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበር /በገበያ ማዕከሉ ጽ/ቤት/
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ መሳለሚያ አጠገብ አማኑኤል ፀጋ የከተማ ንግድ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበር /በገበያ ማዕከሉ ጽ/ቤት/ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112734327
  • Website
  • Deadline06 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-07 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

አማኑኤል ፀጋ የከተማ ንግድ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘው አክሲዮን ማህበራችን ከ 2018 እስክ 2020 ላሉት ሦስት የበጀት ዓመታት ሂሳብ የሚመረምር /ኦዲት የሚያደርግ/ የኦዲት ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

አማኑኤል ፀጋ የከተማ ንግድ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበር /በገበያ ማዕከሉ ጽ/ቤት/


 

የውጭ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ የሚገኘው አክሲዮን ማህበራችን ከ 2018 እስክ 2020 ላሉት ሦስት የበጀት ዓመታት ሂሳብ የሚመረምር /ኦዲት የሚያደርግ/ የኦዲት ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ለሦስቱ በጀት አመቶች የማይለወጥ/የሚፀና ዋጋ በማቅረብ ለመወዳደር የምትፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛላችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት የስራ ቀኖች በስም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ መወዳደርት ችላላችሁ። ጨረታው በሰባተኛው ቀን ማግስት ጠዋት በአራት ሰአት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል። ለሶስቱም በጀት ዓመቶች የሚቀርበው ዋጋ ቫቱን ያካተተ መሆን አለበት።

  1. በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እርሱ በወክለው ህጋዊ አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያለው እና ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
  2. የኦዲት ስራ ለመስራት የሚያስችል ለ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያለው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የምስክር ወረቀቱን ማቅረብ የሚችል
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5. ከዚህ በፊት የኦዲት አገልግሎት ከሰጠባቸው ድርጅቶች ቢያንስ ከ 5 ከማያንሱ ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈፃጸም የምስክር ወረቀት/የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል

 

አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ መሳለሚያ አጠገብ አማኑኤል ፀጋ የከተማ ንግድ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበር /በገበያ ማዕከሉ ጽ/ቤት/

 

ስልክ 0112734327 / 09-11-93-22-72

 

Save Tender