Tender Detail

Tender Details

  • Company በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0468 83 05 33
  • Website
  • Deadline15 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityከሎት1—ሎት2 ለእያንዳንዳቸው ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-15 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች እና መዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት1፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት2፤ የሞተር ሳይክል ጎማና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ግልፅ ጨረታ የማስታወቂያ ቁጥር 04/2018

 

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች እና መዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት1፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት2፤ የሞተር ሳይክል ጎማና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የዘመኑ ግብር የከፈለ እና ስለመክፈሉ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
  4. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
  5. ጨረታው የሚቆየው ከ21/03/2018 ዓ.ም እስከ 6/04/2018 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በሁለት ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በመሙላት ሶ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 4 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ6/04/2018 ዓ.ም ሎት1 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፤ ሎት2 በ8፡30 ታሽጎ በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት የግ/ክ/ን/ አስ/ሥ/ሂደት በግዢ ኬዝቲም ቢሮ ቁ/ር 8 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሎት1—ሎት2 ለእያንዳንዳቸው ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።
  11. አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሰረት አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች /አገልግሎቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ከሎት 1-2 ከእያንዳንዱ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላል።

 

ለበለጠ መረጃ ፡– 0468830533/128

 

የማ/ኢ/ክ/መ/ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender