በአማራ ክልል መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን በመ/ማ/ም/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የሞላሌ ጤና አጠ/ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚውል ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2 የፅዳት ዕቃ፣ ሎት3 ህትመት ውጤቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአማራ ክልል መንግሥት የሰ/ሸዋ ዞን በመ/ማ/ም/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን በመ/ማ/ም/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የሞላሌ ጤና አጠ/ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት የሚውል ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2 የፅዳት ዕቃ፣ ሎት3 ህትመት ውጤቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።
- ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና በዘርፉ የሚሰማሩ
- የንግድ ፈቃዳቸው የታደሰና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸው ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚገዙት የእቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከሞላሌ ጤና አጠጣቢያ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባቀረበው ዋጋ ላይ ድምር 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት /ሲፒኦ/ ቢል ቦንድ የከፈሉበትን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስለዚህ ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ/በፖስታ ውስጥ በማድረግ የሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን ለብቻው በማሸግ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሞላሌ ጤና ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን (ቅዳሜና ዕሁድ) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ 011 622 02 82/ 0912 10 10 68/0911 11 08 55/0920 56 36 25 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ክልል መንግሥት የሰ/ሸዋ ዞን በመ/ማ/ም/ወ/ጤ/ጥ/ፅ/ቤት
