Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት
  • Address የሰሜን ሸዋ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 681-34-10
  • Website
  • Deadline15 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ እና ለሎት 2. የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
  • opening date2025-12-15 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials

በአብክመ/ገ/መ/ኮ/ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በአብክመ/ገ/መ/ኮ/ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር መለያ ቁጥር TIN ያላቸው
  2. ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆኑ ሰዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃና ናሙና ማቅረብ አስፈላጊ ሲሆን ለጽህፈት መሳሪያም ሆነ ለጽዳት እቃ ጨረታው ሰነዱን ሲገዙ ማየትና መረዳት ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አጠቃላይ ማጓጓዣና የሰራተኛ ጉልበትችለው ገቢ ማድረግ የሚችሉና ለሚያቀርቡት እቃ የጥራት ዋስትና መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ የስራ ሂደት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ግዥው ከ20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ መ/ቤቱ ከክፍያው ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 50% ቆርጠን የምናስቀር መሆኑን እናሳውቃለን።
  8. አሸናፈው ውል ገብቶ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ መሰረት በአግባቡ ሞልተው በፖስታ በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ጨረታው በጥቅል መሆኑን አውቀው ዝርዝሩን በሙሉ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ማለት ውድድሩ በጥቅል ዋጋ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡
  11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ወይም አይገደድም፡፡
  13. የጨረታው መከፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ፡- 011 681-34-10/41681501 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት

 

Save Tender