Tender Detail

Tender Details

  • Company የዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የህብረተሰብ ልማት ማህበር
  • Address በምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913117325
  • Website
  • Deadline06 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Accounting & Auditing , Finance

ዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የህብረተሰብ ልማት ማህበር እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 የበጀት ዓመት ያንቀሳቀሰውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ በተሻሻለው የሂሳብ አሰራር ዘዴ /IPSAS/ በመቀየር የኦዲት ስራውን በሚሰሩና ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ባላቸው የሂሳብ አዋቂዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሶስት ዓመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል።

የዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የህብረተሰብ ልማት ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የህብረተሰብ ልማት ማህበር እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2025 የበጀት ዓመት ያንቀሳቀሰውን የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ በተሻሻለው የሂሳብ አሰራር ዘዴ /IPSAS/ በመቀየር የኦዲት ስራውን በሚሰሩና ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ባላቸው የሂሳብ አዋቂዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሶስት ዓመት ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የሚጠበቀውን መስፈረት በማሟላት ህጋዊ እውቅና ያላቸው አማካሪዎች፡-

1ኛ በውጮቹ አቆጣጠር በ2025 ዓ.ም የተንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን 3.5 ሚሊዮን ብር የሚደርስ

2ኛ የሂሳብ ሰነዶች በፋይል ቦክስ ደረጃ እስከ 4 የሚደርሱ መሆናቸውን ስንገልጽ በመስፈርቱ መሰረት ህጋዊ ኦዲት ለማስደረግ እንዲቻል ከዚህ በታች ዝርዝር መስፈረት አስቀምጠናል።

1ኛ በዘርፉ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ማስረጃ የሚያቀርቡ ሆነው የስራ ልምድ ቢያንስ 5 ዓመት ያላቸውና በዚህ ሙያ የታደሰና ህጋዊ የሆነ የሙያ ፍቃድ ኖሯቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለመኖሩ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2ኛ የአገልግሎት የግዥ ዋጋ ለቫት የሚያጋልጥ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3ኛ ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የሰነድ ማስረጃ ኦርጅናሉን ከኮፒ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል

4ኛ አሸናፊው ተጫራች ስራውን የሚያከናውነው በአማራ በብሔራዊ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ መርጦለማርያም ከተማ በመገኘት ይሆናል።

5ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመጣጣኝ ዋጋ ከጨረታ ፖስታው ጋር በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6ኛ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በአካል በመገኘት/በኢሜል አድሬስ/ በመጠቀም የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታው እሁድን ሳይጨምር በ8ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።

7ኛ የጨረታው አሸናፊ የሚመረጠው በተወዳዳሪዎች በሚሞላው ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል በሚሰጠው የነጥብ ድምር ውጤት ይሆናል።

8ኛ አሸናፊ ጨረታውን በአሸነፈ በሶስት ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት

9ኛ የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት ኮፒና ኦርጅናል ሰነዱን በተለያየ ፖስታ በማስገባት በአንድ ማጠቃለያ ፖስታ በማድረግ በህጋዊ ማህተም በመርገጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ወይም በተወካያችን አማካኝነት በስልክ አረጋግጠው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

10ኛ ልማት ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

የጨረታ ሰነዱ ከሚጠይቀው መስፈረት ውጭ መሙላት እንዲሁም መሰረዝ /መደለዝ/ የተከለከለ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0913117325 ወይም 0910622251 ይደውሉ።

 

የዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የህብረተሰብ ልማት ማህበር

 

Save Tender