የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል ሎት1፡- የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት3፡ ቋሚ የቢሮ እቃ (ፈርኒቸር)፣ ሎት4፡- የፅዳት እቃ እና ለሎት5 ፡- የወንበርና እና ኮፒውተር ጥገና በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ደብረብርሃን/ክ/ሙ/ብ/ም/ማ/ማ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡድን
የብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን ክላስተር የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውል ሎት1፡- የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት3፡ ቋሚ የቢሮ እቃ (ፈርኒቸር)፣ ሎት4፡- የፅዳት እቃ እና ለሎት5 ፡- የወንበርና እና ኮፒውተር ጥገና በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
-
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200.000 (ሁለት መቶ ሺ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደብረብርሃን ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ19/3/208 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) በጨረታ ሰነዱ የተገለጸውን ሎት 1፡- የጽሕፈት መሣሪያ ብር 8,000 (ስምንት ሺ)፣ ሎት2፡- የኤሌክትሮኒክስ ብር 3,000 (ሶስት ሺ) ሎት3፡-ቋሚ የቢሮ እቃ ብር 3,000 (ሶስት ሺ)፣ ሎት4፡- የፅዳት እቃ ብር 500 (አምስት መቶ ) ሎት5 የወንበርና እና ኮምፒውተር ጥገና ብር 2,000 (ሁለት ሺ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በደብረብርሃን ክላሰተር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃ ክላስተር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ግዥ ፋይናንስና ለንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 እስከ 16ኛው ቀን ማለትም በ4/4/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም በ4/4/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ዕለት የሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈፅመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሰረት በጥቅል (ሎት) ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሀ) በጨረታው ለመሳተፍ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በአካል ቢሮ ቁጥር 07 ወይም 011 637 66 58/59 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አድራሻ ሼል ኦሬንታል ካፌ ፊት ለፊት አቶ ብሩክ ነጋሽ ሕንፃ ላይ፡፡
የደ/ብርሃን/ክ/መ/ብ/ም/ማ/ማ/ግ/ፋ/ን/አሰ/ቡደን
ደብረብርሃን
