Tender Detail

Tender Details


በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Abbay Basin Administration Office (አባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት)


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ.ቤ.አስ.ጽ/01.1/2018

 

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የጨረታው ሰነድ የሎት (lot) መለያ

  • ሎት - 1. የደንብ ልብስ
  • ሎት - 2 የላቦራቶሪ እቃዎች እና ኬሚካል
  • ሎት -3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት -4 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት -5 የግብርና ግብዓት

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፋ የተሰማሩ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 19 መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት- 01 ደንብ ልብስ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት- 02 የላብራቶሪ ኬሚካል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • ሎት 03 የጽዳት ዕቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያዎች ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት 04 ኤሌክትሮኒክስ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት 05 የግብርና ግብዓት ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)

በአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማሰያዝ አለባቸው፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ እና በድርጅቱ ማህተም በተደረገበት ፖስታ እያንዳንዱ ፖስታው ላይ ተጽፎ ባህር ዳር ብልጽግና ጽ/ቤት ጎን ከሚገኘው የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅቦታል።
  2. የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። የተጫራቾች ወይም ተወካዮች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  3. የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583216896 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት /ባህር ዳር/

 

Save Tender