Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ
  • Address ፒያሳ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ዋስትና የነቢያ ማዕከል ህንጻ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7-03 የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጎን) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-833-25-01
  • Website
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Vehicles Rent , Laboratory Equipment And Chemicals , Electronics Materials , Vehicle tire

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

አመታዊ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ጨረታ

 

የግዥው መለያ ቁጥር፡- AACAHB-PPAD-NCB-Recurrent & Other-Budget-001/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

ምድብ

የአገልግሎቱ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት አንድ

አመታዊ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት

90,000.00

ሎት ሁለት

የላብራቶሪ ግብዓቶች

5,000.00

ሎት ሶስት

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (የውሃ ማጣሪያ)

15,000.00

ሎት አራት

የተሽከርካሪ ጎማ

20,000.00

ሎት አምስት

ቦርሳ

80,000.00

 

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number ያላቸው መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሎት አንድ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ሲፒኦ (CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ (Bank guarantee) በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በግዥና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ያሉ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬት እስከ 10ኛው የስራ ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነዳቸውን የፋይናንስ ዋና እና አንድ ኮፒ እንዲሁም የቴክኒክ ሰነድ ዋና እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  8. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተምና ፊርማ አድርገው ካላቀረቡ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. ቢሮው በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአገልግሎት ፍላጎት መጠን ላይ ከውል በፊት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፤
  10. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 ቀናት ነው።
  11. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡35 ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአትና ቦታ ይሆናል፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

 

አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ዋስትና የነቢያ ማዕከል ህንጻ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7-03 የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት (ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጎን)

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-833-25-01

 

የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

 

Save Tender