Tender Detail

Tender Details

  • Company መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር
  • Address ሲዳሞ ተራ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112-31-31-47
  • Website
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security25,000.00
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት /ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር


የጨረታ ማስታወቂያ

ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል የሕንፃ ቦታ ኪራይ ጨረታ

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት /ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት/ የሚውል ቦታን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በአከሲዮኑ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረግ መርካቶ ሲዳሞ ተራ የማኅበሩ ሕንፃ
  2.  በሚገኝበት 4ኛ ፎቅ ላይ ዘወትር በሥራ ቀናት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ጨረታው በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒአ መተሳሰብ ለእድግት ጠቅላላ ንግድ አከሲዮን ማኅበር ስም አሠርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አከሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር M433 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0112-313147/ 0112-313237/0118-722926 ወይም በአካል ሲዳሞ ተራ መተሳሰብ የገበያ ማዕከል መጠየቅ ይችላሉ።

መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር

Save Tender