Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ዋናው መስሪያ ቤት አራት ኪሎ አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Phone: 0111555230
  • Websitehttps://ethbspe.org/en_US/
  • Deadline30 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10,000 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-30 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለሥራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ሰማያዊ እስክሪብቶ ብዛት 10,000፣ ቁርጥራጭ ጨርቅ (Rag) ብዛት 5,000 ኪ.ግ እና የእጅ ጓንት አጠቃላይ ብዛት 850 (የቆዳ ጓንት ብዛት 250 ጥንድ፣ የሹራብ ጓንት ብዛት 100 ጥንድ እና የፕላስቲክ ጓንት ብዛት 500 ጥንድ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 005/18

 

ድርጅታችን ለሥራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ሰማያዊ እስክሪብቶ ብዛት 10,000፣ ቁርጥራጭ ጨርቅ (Rag) ብዛት 5,000 ኪ.ግ እና የእጅ ጓንት አጠቃላይ ብዛት 850 (የቆዳ ጓንት ብዛት 250 ጥንድ፣ የሹራብ ጓንት ብዛት 100 ጥንድ እና የፕላስቲክ ጓንት ብዛት 500 ጥንድ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሽያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችለሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡

ጨረታው በ21/4/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምግማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴከኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ስልክ ቁጥር፡- 011-1-55-52-30

ድረ-ገፅ (www.ethbspe.org)

Berhanena Selam Printing Enterprise

አዲስ አበባ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

 

Save Tender