በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ማለትም ከተማ አስተዳደሩ በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ማለትም ሎት 1 ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ፤ ሎት 2 ፈርኒቸር፤ ሎት 3 የምህንድስና መሳሪያ /ቶታል ስቴሽን፤ ሎት 4 የኤሌክትሪክ እቃዎች (ዘመናዊ ፓውዛ) ፤ ሎት 5 የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣ ሎት 6 የባህርዛፍ አጣና እንጨት፤ ሎት 7 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች ግዥ እንደሚፈፅም ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎች ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ማለትም ከተማ አስተዳደሩ በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የቋሚ እና አላቂ እቃዎች ማለትም ሎት 1 ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ፤ ሎት 2 ፈርኒቸር፤ ሎት 3 የምህንድስና መሳሪያ /ቶታል ስቴሽን፤ ሎት 4 የኤሌክትሪክ እቃዎች (ዘመናዊ ፓውዛ) ፤ ሎት 5 የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት፣ ሎት 6 የባህርዛፍ አጣና እንጨት፤ ሎት 7 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል እቃዎች ግዥ እንደሚፈፅም ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎች ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ላሉት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 300 ብር /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ገቢ መሰብሰቢያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000 (አስር ሺህ) በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ18/3/2018 ዓ.ም እስከ 2/4/2018 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የጨረታውን አይነት በመግለጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና የድርጅቱን ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና ፈርማ በመፈረም ማስታወቂያው ከወጣበት ከ18/3/2018 እስከ 3/4/2018 ዓ.ም የካላንደር ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ3/4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል በሮ ቁጥር 32 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በጥቅል / ሎት ወይም በነጠላ የማወዳደር መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 13 20 801 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ እቃ የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይቀየራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ከቫት በፊት ከነቫቱ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በሌለው መልኩ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፈው ተጫራች ጋር ውል ከመፈፀሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 30% (ሰላሳ በመቶ) መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚገዙት ሰነዶች ከሰነዱ ጋር ከቀረበው የግዥ ሰነድ ጋር አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የስራ ቦታ ዓለም ከተማ
አድራሻ ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር/ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0111320801/395
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት
