Tender Detail

Tender Details

  • Company ኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንደስትሪ አ/ማህበር
  • Address ሱሉልታ ልዩ ቦታ ኮካ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-45-31-07-80
  • Websitehttp://www.elemtu.com
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

ኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንደስትሪ አ/ማህበር

ኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንደስትሪ አ/ማህበር


 

ኤሌምቱ ኢንትግሬትድ ወተት ኢንደስትሪ አ/ማህበር ያገለገለ መኪና ሽያጭ የጨረታ ሰነድ

 

  1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ ዘወትር በስራ ቀን ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ 3፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00-11:00 እንዲሁም ቅዳሜ 13:00 -6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ድርጅቱ በሚገኝበት ቦታ ሱሉልታ ልዩ ቦታ ኮካ ከድርጅቱ ገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የገዙበትን የገንዘብ ደረሰኝ በመያዝ ተሽከርካሪውንና ለተሽከርካሪው ተገዝተው በስቶር የሚገኙ ኦርጂናል መለዋወጫዎችን በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15/100 ስሌት ታሳቢ በማድረግ በተራ ቁጥር 5 በተገለፀው መሰረት ተፈፃሚ መሆን አለበት።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ተሽከርካሪዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅፅ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ (ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት ተ.ዕ.ታ 15/100 እና ጠቅላላ ድምር) በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታዎች ላይ ብቻ መሞላት አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  6. ማንኛውም ተጫራች ለመሳተፍ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል:: ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው እንደታወቀ በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን የአሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካሸነፌበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል::
  7. ተጫራቾች የሚያሥይዙት C.P.O በድርጅቱ ስም የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሹፍኔ ወይም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሹፉኔ ቅርንጫፍ ብቻ መዘጋጀት አለበት።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ተሽከርካሪ የሚገዙበት ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በፖስታ በማሸግ የጨረታዉ ሰነድ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 29/2018 ዓ.ም ድረስ ሱሉልታ በሚገኘዉ ድርጅቱ ዋና ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  9. ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  10. ጨረታው ሕዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት መኪናዉ ባለበት ቦታ ላይ ይከፈታል።
  11. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው መወዳደሪያ ዋጋ በጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ድርጅቱ የጨረታዉን ዉጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ማግለል አይችልም።
  13. አሽናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በውስጥ ማስታወቂያ በተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ዉስጥ ተሽከሪካሪዉን ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመክፈል በራሱ ወጪ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህን ባያደርጉ ጨረታዉ ተስርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያለምንም ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ በድርጅቱ ገቢ የሚደረግ ሲሆን ተሽከርካሪዉ ድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  14. የጨረታው ዉጤት አሸናፈ ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ የሽያጭ ዉል እንደተደረገ ይቆጠራል። በመሆኑም የመንግስት ግብር እና ስም ማዞሪያን ጨምሮ ማንኛዉንም አይነት ወጪዎችን ገዢ የሚሸፋን ይሆናል።
  15. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-45-31-07-80 ወይም 09-93-12-00-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

ተ.ቁ

የተሽከርካሪ አይነት

የተሰራበት ሐገር

የተመረተበት ዘመን

ሻንሲ ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ ከታክስ በፊት

የተጫራቹ ዋጋ 15/100 ተ.እ.ታክስን ጨምሮ

1

የጭነት

ህንድ

2006

MAT374415C9L00182

500,000.00

 

 

E-mail: Meazanat2007@gmail.com Website: www.elemtu.com

Tel.0111-8696-71/0111-868317 or Mobile: 09-55-80-43-91/0993120007

 

Save Tender