የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/02/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TB/FP/NCB/02/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት 1፡- ፈርኒቸር ሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
ሎት 1፡- ብር 100,000.00 ሎት 2፡- ብር 50,000.00 |
ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ |
ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-6-73-22-05 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
