በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓመት በተያዘው ካፒታል በጀት ሪድዮ ቀበሌ ሰድመተሸን ታንክ ግልጽ ጨረታ ወጥቶ እንዲገነባ በደብዳቤ ቁጥር 544/11/02 በቀን 10/03/2018 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ በጠየቁት መሰረት መ/ቤታችን በግንባታ ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 04/2018
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 ዓመት በተያዘው ካፒታል በጀት ሪድዮ ቀበሌ ሰድመተሸን ታንክ ግልጽ ጨረታ ወጥቶ እንዲገነባ በደብዳቤ ቁጥር 544/11/02 በቀን 10/03/2018 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ በጠየቁት መሰረት መ/ቤታችን በግንባታ ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የንግድ ፍቃድ ያለው ተቋራጭ WWC/BC ደረጃ- 8 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት/
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ የቫትና የቲን ምዝገባ ምስክር ወረቀት መረጃ ኮፒዎችን ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከሚመለከታቸው አካላት የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱ ሲመለስ 1 /አንድ/ ኦርጅናልና 2 /ሁለት/ ኮፒ በተለያየ በታሸገ ፖስታ እና የፋይናንሽያሉንም ሆነ የቴክኒካሉን ለየብቻ በመለየት እንዲሁም ሁሉንም በአንድ እናት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት መቅረብ አለበት፣
- የጨረታ ማስከበሪያ በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠው ሲፒኦ /CPO/ certified payment order/ ገብቶ መቅረብ አለበት፤
- የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግ/ክ/ን/አ/ር ሥራ ሂደት ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት በመቅረብ አንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 300 / ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ከማቅረባቸው በፊት በራሳቸው ወጪ ስራው የሚሰራበትን ቦታ (ሳይት) ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፣
- ቀደም ሲል በወረዳ ውስጥ ማንኛውንም ጨረታ ተጫርተው አልፎ በተባለው/ውል በገባው መሰረት ግንባታ ያላጠናቀቁት ለጨረታ መሳተፍ አይችሉም፤
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡበት ማንኛውም መረጃ ላይ የድርጅቱ ማህተም የስራ አስኪያጅ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፣
- አሸናፊው ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዥ ፍቃደኛ የሆነ፤
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21/ሃያ አንድ/ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ22ኛው ቀን ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- የቅድመ ክፍያ 20% (Advance payment) የሚፈልግ ተቋራጭ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትናን ከታወቀ ባንክ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የጨረታ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን ይሆናል፤
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0911053990/0917686362
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
