በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጀ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጀ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባቢነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከላይ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው መ/ቤት ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ና ፋይናንሻል እንዲሁም ስፔስፊኬሽ ለወጣላቸው ዕቃዎች የፋይናንሻልና የቴከኒከ ሰነድና ሲ.ፒ.ኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየርላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 45 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሰ.ፒ.ኦ በመያዝ በ 15 ቀናት ውስጥ ዕቃውን አጠናቀው ለማቅረብ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፋይናንስ፣ የቴክኒካል ግምገማና ሲ.ፒ.ኦ ፖስታ በሎት ተለይቶ መቅረብ አለበት።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-221-9988/ 046-220-03-26 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
