Tender Detail

Tender Details


በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የሚውል መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች (መሳሪያዎች)፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የሚውል መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች (መሳሪያዎች)፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

•        ሎት 1 የመድኃኒት ግዥ፣ ሎት ምድብ 01/2018

•        ሎት 3 የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ኤጀንቶች ግዥ ሎት ምድብ 03/2018

•        ሎት 4 የአላቂ ቢሮ እቃ እስቴሽነሪ ግዥ፣ ሎት ምድብ 04/2018

•        ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት ምድብ 05/2018

•        ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት ምድብ 06/2018

•        ሎት 7 የህትመት ግዥ፣ ሎት ምድብ 07/2018

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

•        በሥራ መስኩ ሀጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣

•        የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

•        ተጫራቶች ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው። ቼክ ተቀባይነት የለውም፡፡

•        የጨረታ ሰነዱ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በማግስቱ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናትን በመጠቀም የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

•        ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ፋይናንሻልና ቴክኒካል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

•        ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡

•        መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በቢሮ ቁጥር 110 በአካል በመገኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender