Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline19 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityአምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00)
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ እና ህንፃ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC-2) ለየሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የያቤሎ፣ ነገሌ ቦረና፣ ሚዛን አማን፣ ደብረ ማርቆስ እና ጎሬ መቱ ኤርፖርቶች የፖሊስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራ (Construction of Police residence at regional airports, Yabello, Negele Borena, Mizan Aman, Debre Markos and Gore Metu) ለማሠራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T 587

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ እና ህንፃ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC-2) ለየሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፍቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የያቤሎ፣ ነገሌ ቦረና፣ ሚዛን አማን፣ ደብረ ማርቆስ እና ጎሬ መቱ ኤርፖርቶች የፖሊስ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራ (Construction of Police residence at regional airports, Yabello, Negele Borena, Mizan Aman, Debre Markos and Gore Metu) ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለሥራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T587 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሁሉም ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 180 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታኅሣሥ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-8025

ኢ-ሜይል፡ WoldeM@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender