Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥ/ጎጃም አስተዳደር ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት1፡- የጽ/መሳሪያ እቃዎች ሎት2፡- የጽዳት እቃዎች 3፡- የግንባታና የውሃ እቃዎች ሎት4፦ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት/ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2018

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥ/ጎጃም አስተዳደር ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት1፡- የጽ/መሳሪያ እቃዎች ሎት2፡- የጽዳት እቃዎች 3፡- የግንባታና የውሃ እቃዎች ሎት4፦ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት/ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርበታል።

  1. የተሰጣቸው የንግድ ሥራ ፈቃድ 1 ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ቲን ነምበር/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎችን በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሥራውን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መሥራት የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገውና ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚፈለገው ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታው ላይ ዋናውንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸው።
  5. እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሞሉት በነጻ ገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡ ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1፡- 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት2፡- 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት3:- 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት4፡- 20,000.00/ ሃያ ሺህ ብር/ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታው ጋር ለብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታ ሸ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ሲሆን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ከሎት1 እስከ ሎት 4 ድረስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለሁሉም የእቃ አቅርቦት ተወዳዳሪዎች 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን /ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. አቅርቦቱን ለማቅረብ ውሉን ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ ከሎት1 እስከ ሎት 3 በገቡት ውል መሰረት በ30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ካሸነፉበት ዋጋ የዋጋ ልዩነት ቢኖር ምንም አይነት ጭማሬ የማናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ተጫራቹ ከከልላችንም አልፎ በወረዳችንም የእቃ አቅርቦት ሥራውን ለመሥራት ችግር የሌለበት መሆን አለበት፡፡
  10.  በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  11.  ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  12.  የተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን አለበት፡፡
  13.  አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን ለእቃ አቅርቦት 10% ለግንባታ ዘርፍ ሥራዎች (25%) ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ እና ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  14.  ለሁሉም የእቃ አቅርቦት ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለግንባታው ዘርፍ ሥራዎች 60 /ስልሳ ቀናት/ ሲሆን ለእቃ አቅርቦት ደግሞ 40 /አርባ ቀናት/ መሆኑን መገንዘብ አለበት፡፡
  15.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከመሙላታቸው በፊት በጽ/ቤቱ የተቀመጠውን ናሙና (ሳምፕል) ማየት አለባቸው፡፡
  17.  ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0582470509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የሸበል በረንታ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት

 

Save Tender