የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
ድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር – 02/2018 ዓ/ም
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርቡት ተሸከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸዉና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክከል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋዉን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት፤ ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር-03 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ- -14/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ - 29-/-02-/2018 ዓ.ም ጎጃም ጥገና ጽ/ቤት ደብረ ማርቆስ ከተማ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ -29- /-03-/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ29/03 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ደህረ ገጽ www.arca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
(ደብረ ማርቆስ)
