Tender Detail

Tender Details


የቦንጋ እጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስና የደብል ካፕ ፎርድ መኪና እና የሎንግ ቤዝ መኪና ጎማ እንዲሁም ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

የቦንጋ እጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 0.1/2018/

 

የቦንጋ እጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል በ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስና የደብል ካፕ ፎርድ መኪና እና የሎንግ ቤዝ መኪና ጎማ እንዲሁም ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀምና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

1.     ሎት -01 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ

2.     ሎት-02 የደንብ ልብስ ግዥ

3.     ሎት-03 የደብል ካፕ ፎርድ መኪና ጎማ ግዥ

4.     ሎት-04 የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና

በዚሁ መሠረት

1)     በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

2)     ሕጋዊ የኮንስትራክሽን የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3)     የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡

4)     የተጨማር እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5)     የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (Tin No) ያላቸው

6)     በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

7)     የጨረታ ማሰከበርያ ለሎት-01 ብር 4,000.00 እና ለሎት-03 ብር 5,000.00 ለሎት-04 10,000 በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01 ለሎት 02 ለሎት 03 ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሎት 04 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በማዕከሉ ባንክ አካወንት ቁጥር 1000099955361 በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከማዕከሉ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላል።

8)     ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የግዥን እንዲሁም ለ21 ቀናት የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገናን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ ተፈላጊ መረጃዎች ጋር በፖስታ በማሸግ በቦንጋ እፅ/ዘር/ጥ/ቁ/ም/በማዕከል የግዥና ክፍያ ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ወስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9)     የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ሲመልሱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

10)            ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡

11)            ጨረታው ለግዥዎች በ16ኛ ቀን ለውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና በ22 ቀን ከሰዓት 08፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ 09:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል የተጠቀሰው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

12)            በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማብራሪያ መጠየቅ የሚችለው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ (10) ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፣፣

13)            ውጤት አስመልክቶ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለሰባት /07/ ተከታታይ ቀናት ብቻ ነዉ፡፡

14)            የውሃ ፓምፕ እድሳትና ጥገና ተጫራቾች አሸናፊው ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ /Performance bond/ ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት፡፡

15)            ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

16)            የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርቦ ውል በመግባት የሚያቀርባቸው ዕቃዎች እስከ ማዕከሉ ግቢ ድረስ ማቅረብ አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በውሉ መሰረት ዕቃዎች ባይቀርቡ ስራው ቢስተጓጎል በግዥ ኤጀንሲ ደንብ ወይም በኮንስትራክሽን ህግ መሰረት ውል ተቀባይ እንዲጠየቅ ይደረጋል።

17)            በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ነገርግን በእያንዳንዱ ሎት ላይ የተካተቱ ሀሳቦች በጋዜጣ አንደወጣ ይቆጠራል፡፡

18)            ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917476163 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

የቦንጋ አጽዋት ዘር ጥራት ቁጥጥርና ምርመራ ማዕከል

Save Tender