የአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥ/ጽ/ቤት
ድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማሽነሪ እና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ቁጥር 02/2018 ዓ/ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ከንስትራክሽን ኤጀንሲ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገነቡ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች እና ለመንገድ ጥገና ስራ ለሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና ለክላስተር ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት፣ ለገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስድሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር -03 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ14/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/03/2018 ዓ.ም ሰ/ሽዋ ጥገና ጽ/ቤት ደ/ብርሀን ከተማ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂላቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ አፊሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 29/03/2018ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራክሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ወይም ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በ29/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላክ ወይም በስልከ ቁጥር 058-320-55-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ወይም በኤጀንሲው ደህረ ገጽ www.arrca.gov.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
የሰ/ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
