በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደ/ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
የደንብ ልብስ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አይኢ.ደብ ቅ/ግጨ /0/2018
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደ/ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ።
• ሎት 1. የቆዳ ጫማ
• ሎት 2 የፕላስቲክ ቦት ጫማ
• ሎት 3 የተዘጋጁ ልብሶች
• ሎት 4. ብትን ጨርቅ
• ሎት 5. የደንብ ልብስ የስፌት አገልግሎት
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የተሰማሩ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸዉና የተጨማሪ እሴት /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። ጨረታው ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ግዴታ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። ነገር ግን ከሁለት መቶ ሺህ ብር በታችም ቢሆን ግዴታ የቲአቲ (TOT) ተመዝጋቢ መሆን አለበት በፓድ ደረሰኝ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. በጨረታው የሚቀርበውን ሁሉንም ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመክፈል በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በመስሪያ ቤቱ አካውንት ገቢ አድርገው የባንከ አድቫይዝ ማስያዝ ይችላሉ ከዚህ ውጭ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ 2% የሚያሲዙት ቫትን አካቶ ነው፤ ግዥው ከ20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ኢንተርፕራይዙ TOT /3% የሚሰበስብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚያቀርቡበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በመጻፍ ፈርመው ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት የደንብ ልብስ ግዥ ግልፅ ጨረታ” ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም ይከፈታል።
8. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ TOT) 15% ይጨምራል፡፡
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. አሸናፊው ተጫራች ሁሉንም ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ኢንተርፕራይዙ በሚገኝበት ቦታ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
ሁሉም ጨረታ በሎትና በድምር ዋጋ በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የሁሉንም እቃ ዋጋ መሙላት የሚጠበቅበት ሲሆን ሳይሞላ የተዘለለ እቃ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116375030/0932497118 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ::
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ
