በደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለመልሶ ማቋቋሚያ አገልግሎት የሚውሉ ከዞን ማዕከላት ወደ የተለያዩ ወረዳዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደ/ኢት/ያ/ክ/መንግሥት አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 133/18
የማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
በደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለመልሶ ማቋቋሚያ አገልግሎት የሚውሉ ከዞን ማዕከላት ወደ የተለያዩ ወረዳዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዣ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የአቅራቢነት ምዝገባ እና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀን የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋቸው 40,000 ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ15ኛው ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በዲላ ከተማ ከሚገኘው ግብርና ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል ፡፡
- ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461310134
ማሳሰቢያ፡- የምግብና ምግብ ነክ-ያልሆኑ ቁሳቁሶች የማጓጓዣ ትራስፖርት አገልግሎት ግዥ ጫኝና አውራጅን ጨምሮ ይሆናል።
በደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
