በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ዙር ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሳተም ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሁለተኛ ዙር ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሳተም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ:-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያላቸው ሆነው፣
- የዘመኑን ግብር በመክፈል የታደሰ ንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ
- ገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር (Supply List) ውስጥ ያላችሁ ወይም የዕቃ አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት መረጃ የሚያቀርብ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ሰነድ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 10,000 ብር (አስር ሺ ብር) በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና አንድ የኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይቀርባል፡፡
- ተጫራቾች የሰጠናችሁ ሁሉንም ሰነድ ሙሉ አድራሻ የተገለጸበት ሆኖ በሚመለከተው ባለስልጣን (ህጋዊ ውክልና ባለው አካል) የተፈረመበትና በማህተም ተረጋገጦ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 የስራ ቀናት በአንድ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ እስከ 16ኛው ቀን በማቅረብ ጨረታውን የያዘው ሳጥን በዚያው እለት ከጠዋቱ 3:30 ተዘግቶ ከቀኑ 4፡00 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያግድም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- የጨረታው ውድድር በአይነት መሆኑን ይታወቅ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111150199/0910190070 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
