ዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አ አርሶ አደሮች በያዘናው ምርት ዘ ዘመን 201 2018 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከሱራ ኮዮ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገሪ ራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ/ዳፕ/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨ ስለሆነም ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር 008/2018
ዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዘናው ምርት ዘመን 2018 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከሱራ ኮዮ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ/ዳፕ/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾት ከድርጅቱ የማራገሪ ጣቢያዎች ዎችን ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሰረት
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ደርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርያለው/ያላት/፤
2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. ከዚህ ቀድሞ በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ሰለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፤
4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤
5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ስፒኦ /CPO/ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆንማንኛውምድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤
7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 2,400 /ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል /በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሠሌዳ ቁጥር የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር/1000 /አንድ ሽህ ብር/በመከፈል ከዳሞታ የወላይታ ገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
9. የጨረታውን ሰነድ በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ /ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።
10.ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል ። ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
11.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12.የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት በመስፈርቱ መሠረት ማሸነፉ ሲረጋገጥ በዩኒዬን ማስታውቂያ ቦርድ የሚገለፅ ይሆናል።
አድራሻ ፡- ወላይታ ሶዶ መናሐሪያ ፊት ለፊት ወደ ኦቶና በሚወስደው አስፋልት ላይሙሐባና ቻይና ጋራጅ ጎን ይገኛል።
ስልክ ቁጥር:-0465510642/0910432549/0966261800
ፋክስ:- 0465522955
ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
