የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ቂጤ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ክልል ቂጤ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ የቁጠባ ቤት ኩሽና እና ሽንት ቤት ለማስገንባት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ቂጤ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ክልል ቂጤ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አካባቢ የቁጠባ ቤት ኩሽና እና ሽንት ቤት ለማስገንባት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
- ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆነ ድርጅት
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች እና ክሊራንስ ከግብር መ /ቤት ያቀረበ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ምትችል
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
- የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፈደል መግለጽ አለባቸው። በፈደል እና በአሀዝ መካከል ልዩነት ካለው በፈደል የተገለጸው ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሦስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ሰንድ (1) ኦርጅናል እና ሁለት (2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅርብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጐ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፍ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘገጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ሥራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤቱ በደ/ቤ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0966886973 / 0910997747/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
ጽ/ቤቱ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
