የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎችና ጌጣጌጦችን፡ የጽዳት አገልግሎትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተለ‐ትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎችና ጌጣጌጦችን፡ የጽዳት አገልግሎትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተለ‐ትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
2. አግባብነት ያለውና ከጨረታው አይነት ጋር የሚጣጣም የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
3. በታከስ ባለስልጣን የተጨማሪ ዕሴት ታከስ /VAT/ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
4. የግብር መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
5. የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ አግባብነት ካለው የመንግስት መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡
6. የአቅራቢነት ምዝገባ ላይ ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
7. መ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች ማቅረብ አይቻልም::
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ: ለተሽከርካሪ ጎማዎችና ጌጣጌጦች ለእያንዳንዱ 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ብር፣ ለጽዳት አገልግሎት 15,000/አስራ አምስት/ ሺህ ብር ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በርPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብርብቻ በመከፈል 4ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ለመጫረት ዋጋ ያቀረቡባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
11.ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ/financial proposal/ እና የቴከኒኩን /Technical proposal / ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻም አራቱንም አንድ ላይ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
13. ዘግይቶ የሚመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
14. ተጫራቾች ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አ ን/ስልከ ላፍቶ ከ/ከተማ ሳርቤት በሚገኘው የመ/ቤቱ ግምጃ ቤት ገቢ ካደረጉ በኋላ ከፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
16. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡ አድራሻ፡-አ/አ ን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ሳር ቤት፣የኦሮሚያ ቢሮዎች ያሉበት ግቢ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ነው::
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
