Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251462120120
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲሰ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid Security25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የደንብ ልብሶችንና ጨርቆችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፤ HU/CMHS/NCB/Yedeneb Libs/04/04/2018 BY

 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የደንብ ልብሶችንና ጨርቆችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌደራል ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ web site/ ላይ የተመዘገቡ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  3. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡40 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ 251-46 212-0120

ፋክስ 251-46 220-8755

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

 

Save Tender