Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-637-50-23
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለባለ አንድ ኢንች ኤችዲፒ ቧንቧ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment , Water Pipes And Fittings , Electronics Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች እና ለወረዳው ውሃና ኢነርጂ ልማት ፅ/ቤት ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ባለአንድ ኢንች ኤችዲፒ ቧንቧ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች እና ለወረዳው ውሃና ኢነርጂ ልማት ፅ/ቤት ለግንባታ አገልግሎት የሚውል ባለአንድ ኢንች ኤችዲፒ ቧንቧ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል፤

ስለዚህ፡-የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡-

የዘመኑን የታደሰ የጅምላ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው!

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መሞላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክከል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦርጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማና አድራሻ ተፅፎበት በማሸግ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች እና ባለአንድ ኢንች ኤችዲፒ ቧንቧ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ ቤት የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።

ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፤ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው፤

የጨረታ ሰነዱን በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 መግዛት ይቻላል።

የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትይሆናል።

የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO ብር ለኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለባለ አንድ ኢንች ኤችዲፒ ቧንቧ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ 10% የውል ማስከበሪያ በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-637-5023 ደውለው መረዳት ይችላሉ!

 

የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ደ/ብርሃን

 

Save Tender