Tender Detail

Tender Details

  • Company የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር
  • Address ፒያሣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት የነበረ በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911 80 48 20
  • Website
  • Deadline23 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየዋጋውን 2%
  • opening date2025-11-23 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር ቀጥሎ የተመለከተውን መስፈርት ከሚያሟሉ ተጫራቾች ለጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች የወንድ እና የሴት ጉርድ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር ቀጥሎ የተመለከተውን መስፈርት ከሚያሟሉ ተጫራቾች ለጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች የወንድ እና የሴት ጉርድ ጫማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1ኛ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድና ሥራ ፈቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ የከፈለበትን ኮፒ ማቅረብ የሚቻል።

2ኛ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) የዋጋውን 2% ማስያዝ አለባቸው።

4ኛ/ የጨረታ መወዳደሪያ ዝርዝር መግለጫ (Technical) በፖስታ በማሸግ እንዲሁም የፋይናንሻሉን በአንድ ፖስታ በማድረግ እንደዚሁም የሲፒኦ (CPO) በአንድ ፖስታ በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ ፖስታ በማጠቃለል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

5ኛ/ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ቀን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

6ኛ/ በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ጫማ በራሱ ትራንስፖርት ፒያሣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት የአክሲዮን ማህበሩ ቢሮ ቁጥር 18 በማምጣት ያስረክባል።

7ኛ/ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የወንድም ሆነ የሴት የተለያዩ የጫማ ናሙና ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጫማው መልክና ዓይነት በጥቁር መሆን አለበት።

8ኛ/ ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል።

9ኛ/ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን፡- ፒያሣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት የነበረ በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ይሆናል።

 

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኛች አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender