በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ሪጆ ፓሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት-1 ቋሚ እቃ ፤ ሎት-2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት-3 የጽዳት እቃ፣ ሎት-4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ሪጆ ፓሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆን ሎት-1 ቋሚ እቃ ፤ ሎት-2 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት-3 የጽዳት እቃ፣ ሎት-4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው።
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት 1% ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ የኮምቦልቻ ሪጆ ፓሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት በመክፈል ከ08/03/2018 ዓ.ም እስከ 22/03/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ የኮምቦልቻ ሪጆ ፓሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ 8/03/2018 ዓ.ም እስከ 23/03/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በ23/03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጅ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ5 /አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 551 1296/ 09 52 65 66 28/ 09 21 25 75 10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል። ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅበታል።
- ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል።
- ለሎት 01፣ ለሎት 02፣ ለሎት 03፣ ለሎት 04 ጥራታቸው ኦርጅናል/ መሆናቸውን በባለሙያ ተረጋግጦ ስለሆነ ንብረት ክፍል ገቢ የሚሆኑት ስለሆነም እቃዎቹ በኦርጅናል/ ጥራት ባላቸው እቃዎች መሰረት ሰነዱን መሙላት ይጠበቅባችኋል።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የኮምቦልቻ ሪጆ ፓሊታን ከተማ አስተዳደር የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ክፍለ ከተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የቦርከና ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት
