በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በተፈቀደ የሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያየ ዓይነት የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የቀላል መኪና ጎማና የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል።
የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/ቁ/02/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ በተፈቀደ የሥራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተለያየ ዓይነት የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የቀላል መኪና ጎማና የቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች የንግድ ፈቃዱን በጀርባው ያለውንም ጭምር ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጽ/ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ለእቃ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታ ኮሚቴው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ድረስ በማስገባት ይኖርባቸዋል፤ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ከላይ የተጠቀሰው የጨረታ የመክፈቻ ቀን ካላንደር ዝግ /ቅዳሜና እሁድ/ ከሆነ የመክፈቻው ቀን ለሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ይተላለፋል።
- ጨረታውን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 15,000, ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 2,000፣ የተለያየ ዓይነት የደንብ ልብስ ብር 10,000፣ የስፖርት ትጥቅ ብር 5,000፣ የስፖርት እቃዎች ብር 2500 ለቀላል መኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 15,000 የቀላል መኪና ጎማ ብር 25,000፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ለደህንነት ለባል የመጀመሪያው ሲሆን አስገዳጅ ሆኖ ከተገኘ ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይቻላል።
- ለሁሉም ግዥዎች የውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው አካል የሚያሸንፍበትን እቃ በላሊበላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በራሱ ትራንስፖርት ከሚፈልገው ቦታ ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ጨረታ አሸናፊ ሆነው እንደውላቸው ያላጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ተቋም ዕገዳ የተደረገባቸውን አያካትትም።
- ተጫራቾቹ በጨረታው ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታው የጊዜ ገደብ ከማለቁ ከ3 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾቹ ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 336 1142/ 033 336 1143/ 033 36 11 69 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የላሊበላ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት
