Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓመት አገልግሎት የሚውል አርጅናል ቋሚ እቃዎች ለመግዛት ስለምንፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

 

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓመት አገልግሎት የሚውል አርጅናል ቋሚ እቃዎች ለመግዛት ስለምንፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤ቲን-ነምበር እና አቅራቢ ዝርዝር ዉስጥ መመዝገብ አለባቸዉ።
  2. ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 እንቁላል ፋብሪካ እምቢልታ ሆቴል ከፍ ብሎ ከሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በየእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች እቃዎችን ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማችሁን ፊርማችሁና አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት በጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  8. የማወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሞላት አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸዉ።
  10. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ የእቃዉን ብዛት 20% መጨመር ወይም 20% ከዉሉ በፊት መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
  11. መ/ቤቱ የሚገዛዉን ዕቃ እስከ 6ወር ዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ ተጨማሪ 25% ዕቃ ግዥ መፈፀም ይችላል።
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የዉል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. ተጫራቹ ያሸነፈዉን እቃ የመ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ አለበት።
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አምራች ከሆኑ ከአገርዉስጥ አቅርቦት ጋር በሚወደዳር ጊዜ 3% ልዩ አስታየት ይደረግላቸዋል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 827 8952

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሳ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት

Save Tender