Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አላቂ እቃዎችን መግዛትይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አላቂ እቃዎችን መግዛትይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፦

1. ሎትı፡-እስቴሽነሪ ሎት2 ፡ህትመት ሎት3 ፡-የፅዳት እቃ ሎት4- የደንብ ልበስ ሎት5 -ኤሌከትሮኒክስ ሎት6፡- ለተለያዩ መሳሪያና መፅሃፍትግዥ ሎት7 ፈርኒቸር፡- በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል

2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን /ያላቸው

4.ተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ምዝገባ ምስከር ወረቀት/የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ ላልሆኑ የሚሞሉት ዋጋ 200.000 (ከሁለት መቶ ሺህ) ብር መብለጥ የለበትም፡፡

5.ተጫራቾች ሰነዱን ከበ/ወ/ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁ.10 ማሳታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰአት ቀርበው በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ በመሂ/ 1 ገቢ ማድረግ ወይም በባንክበተረጋገጠ ከፍያ /cpo/ ማስያዝ አለባቸው ::

7.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አርጅናል ብቻ በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ የጨረታውን ሰነድ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: በዚሁ ሰአት የጨረታው ሳጥን ይዘጋል /ይታሸጋል/፡፡

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው/የውክልና ህጋዊ ደብዳቤ በመያዝ /በተገኙበት በዚያኑ ቀን በ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋይናንስ ቢሮ ቁ.10 ይከፈታል፡፡

9. በጨረታው ላይ የሚሳተፈው ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ ወዲያውኑ ውል ፈፅሞ እቃውን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

10. ተጫራቾች ለጨረታው ከተዘጋጀው ሰነድ በተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁ.10 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስ/ቁ 022-472-01-72 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡

11. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

12. ውድድሩ በተናጠል ወይም በጥቅል /በሎት ድምር ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡

13. ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender