Tender Detail

Tender Details

  • Company በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address ሙዱላ ከተማ መናኸሪያ መግቢያ አስፓልቱን ገባ ብሎ ባለው ጽ/ቤት : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0928767961
  • Website
  • Deadline25 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-11-25 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

ጠ/ል/ወረዳ ጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን በማ/ኢ/ክ/መንግስት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ባሉት ቀበሌዎች ላሉት አርሶ አዳሮች በያዝነው 2018 ዓ/ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማረገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ፣ በልግና ለመኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን


 

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

 

ጠ/ል/ወረዳ ጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን በማ/ኢ/ክ/መንግስት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ባሉት ቀበሌዎች ላሉት አርሶ አዳሮች በያዝነው 2018 ዓ/ም በሙዱላ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ለሰብል አብቃይ ቀበሌያት ማረገፊያ ጣቢያዎች ለመስኖ፣ በልግና ለመኸር የአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በዚሁ መሠረት

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሰደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ህጋዊ ሰውነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ ተቋም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣ የተሽከርካሪዎቹን ኢንሹራንስ መድን ዋስትና የዘመኑን ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ ቢችል ይመረጣል፡፡
  4. የጨረታው ተሳታፈዎች ለአስተዳደር እንዲመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 1000 (አንድ ሺህ) ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችል መኪናዎችን ወይም የሠሌዳ ቁጥር ፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በጠምባሮ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን ጽ/ቤት ሙዱላ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡
  8. የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከተታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል ፡፡
  9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለፀው ቦታና ጊዜ ታሽጎ ይከፈታል።
  10. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ:- ሙዱላ ከተማ መናኸሪያ መግቢያ አስፓልቱን ገባ ብሎ ባለው ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0928767961/0910851795

 

በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጠምባሮ ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒየን

 

Save Tender