Tender Detail

Tender Details


የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት1 የፓምፕና ሞተር ከኤሌክትሪክ እቃዎችን ጋር፣ ሎት2 የደንብ ልብስ፣ ሎት3 ኬሚካል እና የኬሚካል እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት1 የፓምፕና ሞተር ከኤሌክትሪክ እቃዎችን ጋር፣ ሎት2 የደንብ ልብስ፣ ሎት3 ኬሚካል እና የኬሚካል እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 ማገኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ 1 ኦሪጂናል እና 1 ኮፒ በአጠቃላይ 2 ሰነዶችን (ኦርጅናልና ኮፒ) በማለት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ22 ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን፣ ነገር ግን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0920208146፣ 0914613590፣ 0989887862 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ውድድሩ በየአንዳንዱ የሎት ጥቅል ድምር ነው።

 

ማሳሰቢያ፡- በሎት 01 ለተጠቀሰው ለሞተርና ፓምፕ እቃዎች ቴክኒካልና ፋይናሽያል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡

 

የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender