በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ለመገልገያ የሚውሉ የህክምና እቃዎች፣ መድሀኒትና ሪኤጀንቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች፣ የስፖርት እቃዎች፣ ህትመት፣ የመኪና ጎማ ግዢ፣ እና የህክምና እቃዎች ጥገና፣ የጥገና ሥራዎች እንዲሁም የሚወገዱ መድኃኒቶችና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ለመገልገያ የሚውሉ የህክምና እቃዎች፣ መድሀኒትና ሪኤጀንቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች፣ የስፖርት እቃዎች፣ ህትመት፣ የመኪና ጎማ ግዢ፣ እና የህክምና እቃዎች ጥገና፣ የጥገና ሥራዎች እንዲሁም የሚወገዱ መድኃኒቶችና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።
በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውንና የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
በየሎት
1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 ብር
2. ኮምፒውተርና ተዛማች እቃዎች 7,500 ብር
3. ጥገና ሥራዎች 4,500 ብር
4. የእስፖርት እቃዎች 1,000 ብር
5. የህክምና እቃዎች ጥገና 1,000 ብር
6. የሚወገዱ መድኃኒቶችና ሪኤጀንቶች 2,000 ብር
7. የህክምና እቃዎች 10,000 ብር
8. መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች 10,000 ብር
9. ህትመት 4,000 ብር
በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (C.P.O) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻችው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ/ኢንቨሎፕ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖረበታል።
- አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ጤና ጣቢያው የአቅርቦት ዝርዝር (ስፔስፍኬሽን) በሚጠይቁ አቅርቦቶች ላይ ባወጣው መሰረት ተጫራቾች ካታሎግን ጨምሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታም ሆነ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (C.P.O) አሸነፋችሁም አለሸነፋችሁም ከ6 ወር በፊት መውሰድ ይኖርባቸዋል 6ወር በኋላ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፈት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 011 893 29 82/011 667 42 37
የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
