የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሃንጋር ቁጥር ስድስት (6) ቱል ሩም ህንፃ ለመገንባት (Construction of Hangar number Six (6) Tool Room Building at Addis Ababa Bole International Airport) ብቃቱን ያሟሉ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T583
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሃንጋር ቁጥር ስድስት (6) ቱል ሩም ህንፃ ለመገንባት (Construction of Hangar number Six (6) Tool Room Building at Addis Ababa Bole International Airport) ብቃቱን ያሟሉ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላና የህንጻ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ በአገር ውስጥ የተመዘገቡና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግስት ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T583 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy)፣ የጨረታ ቁጥር፣ የድርጅቱን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ 80 ተከታታይ ቀናት ነው፡፡
ተጫራቾች ሶስት መቶ ሺህ ብር (300,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ መሆን ይኖርበታል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እሰከ ታኅሣሥ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ውድቅ ይሆናሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
በስልክ ቁጥር: +251-115-17 89 18
ኢ-ሜይል: EskedarG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
