Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ (የሚጫረቱበትን ዋጋ) 5% (አምስት ከመቶ)
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Used Items , Aluminium Supply and Work

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሞጆ ከተማ ቴሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ የብረት እና አልሙኒየም በር እና መስኮቶች ግዢ ፍላጎቱ ላላቸው ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


 

ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሞጆ ከተማ ቴሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች፣ የብረት እና አልሙኒየም በር እና መስኮቶች ግዢ ፍላጎቱ ላላቸው ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ/ድርጅት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት ድርጅት ከሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከህዳር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ላገለገሉ ዕቃዎች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ (የሚጫረቱበትን ዋጋ) 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት አድራሻ የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ጨረታው እየር ላይ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የተጠቀሱት ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ አዳማ ከተማ አሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት አድራሻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ በዕለቱ ህዳር 30 ቀን 2018 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

 

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-211 3967 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

 

Save Tender